Birhan | Spiritual Messages, Teachings & Insights.

Birhan Logo: A stylized representation of the company's name, with vibrant colors and modern design. Explore spiritual messages, teachings of Lord Jesus, insights from ascended masters, and divine guidance from Mother Mary, God, Lord Sananda, and Archangel Michael on Birhan.

ታላቁ መለኮታዊው ዳይሬክተር

D

ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር   |    THE GREAT DIVINE DIRECTOR

የሰባተኛው ዘር ምንጭ    |   Manu of The Seventh Root Race

ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር ጠፈራዊ ፍጡር (Cosmic Being) ነው ። እሱ እንዲህ ይላል ፣“ እኔ ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር በመባል እታወቃለሁ ፣ ምክንያቱም ንቃተ ህሊናዬን ወይም ንቃተ ግንዛቤዬን  ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ዕቅድ የጠፈር ዑደቶች (cosmic cycles) ከማይታወቁ የብርሃን አጽናፈ ሰማዮች ( universes) ጋር በማዋሃድ ነው”።

እናም ፣ ስም የለሹ እግዚአብሔርን በማያወላዉል (ጥብቅ) መመሪያ ሕግ እድርጎ የሚያመልከው ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር በመባል ታወቀ ፣ ምክንያቱም  በማምለክ፣ እርሱም የተመለከ ሆነ እና ከዚያም ተወዳጅ ሆነ። ከዛም ፣ በአጽናፈ ጠፈር ተዋረድ ባለው ጽሕፈት ቤት ፣ ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር  የሚለው ስም የእርሱ የአምላክነት-ማንነት ሆነ።

እሱ ከረጅም ጊዜ በፊት የመንፈስ መነቃቃትን በመሻገሩ በአጽናፈ ጠፈር ደረጃዎች (cosmic levels)  ባሉ የእግዚአብሄር ኣገልግሎቶች እንዲቀመጥ ሆኖዋል እናም  የሰባተኛው ዘር ምንጭ ለመሆን ብቁ አድርጎታል።

መለኮታዊ ዳይሬክተርነት በእግዚአብሔር ዘንድ የንቃተ ህሊና የብቃት ደረጃ ነው። እግዜአብሄር ለሁሉም ህይወት ስላለው ዕቅድ ፍጹም ግንዛቤው ስላለዉና፣ ይህም ግንዛቤው (awareness) በራሱ ውስጥ  አቅጣጫውን ብቻ ሳይሆን፣ የድርጊት አፈፃፀሙን አመክንዮአዊ መደምደሚያዉንም በውስጡ ይይዛል።

ይሄ ትርጉም  በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከተጻፈዉ  ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር ታሪክ ተቀንጭቦ የቀረበ የአማርኛ ትርጉም ነው። This article is a verbatim translation of the English version of a portion from the introduction of THE GREAT DIVINE DIRECTOR at the following  website:  https://sirius-eng.net/liki/vkp_vbn.htm

ተርጓሚ  መስፍን ሃጎስ ተወልደ