የሰባተኛው ዘር ምንጭ | Manu of The Seventh Root Race
ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር ጠፈራዊ ፍጡር (Cosmic Being) ነው ። እሱ እንዲህ ይላል ፣“ እኔ ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር በመባል እታወቃለሁ ፣ ምክንያቱም ንቃተ ህሊናዬን ወይም ንቃተ ግንዛቤዬን ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ዕቅድ የጠፈር ዑደቶች (cosmic cycles) ከማይታወቁ የብርሃን አጽናፈ ሰማዮች ( universes) ጋር በማዋሃድ ነው”።
እናም ፣ ስም የለሹ እግዚአብሔርን በማያወላዉል (ጥብቅ) መመሪያ ሕግ እድርጎ የሚያመልከው ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር በመባል ታወቀ ፣ ምክንያቱም በማምለክ፣ እርሱም የተመለከ ሆነ እና ከዚያም ተወዳጅ ሆነ። ከዛም ፣ በአጽናፈ ጠፈር ተዋረድ ባለው ጽሕፈት ቤት ፣ ታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር የሚለው ስም የእርሱ የአምላክነት-ማንነት ሆነ።
እሱ ከረጅም ጊዜ በፊት የመንፈስ መነቃቃትን በመሻገሩ በአጽናፈ ጠፈር ደረጃዎች (cosmic levels) ባሉ የእግዚአብሄር ኣገልግሎቶች እንዲቀመጥ ሆኖዋል እናም የሰባተኛው ዘር ምንጭ ለመሆን ብቁ አድርጎታል።
መለኮታዊ ዳይሬክተርነት በእግዚአብሔር ዘንድ የንቃተ ህሊና የብቃት ደረጃ ነው። እግዜአብሄር ለሁሉም ህይወት ስላለው ዕቅድ ፍጹም ግንዛቤው ስላለዉና፣ ይህም ግንዛቤው (awareness) በራሱ ውስጥ አቅጣጫውን ብቻ ሳይሆን፣ የድርጊት አፈፃፀሙን አመክንዮአዊ መደምደሚያዉንም በውስጡ ይይዛል።
ይሄ ትርጉም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከተጻፈዉ የታላቁ መለኮታዊ ዳይሬክተር ታሪክ ተቀንጭቦ የቀረበ የአማርኛ ትርጉም ነው። This article is a verbatim translation of the English version of a portion from the introduction of THE GREAT DIVINE DIRECTOR at the following website: https://sirius-eng.net/liki/vkp_vbn.htm
ተርጓሚ መስፍን ሃጎስ ተወልደ