Birhan | Spiritual Messages, Teachings & Insights.

Birhan Logo: A stylized representation of the company's name, with vibrant colors and modern design. Explore spiritual messages, teachings of Lord Jesus, insights from ascended masters, and divine guidance from Mother Mary, God, Lord Sananda, and Archangel Michael on Birhan.

እውነት፣ እግዚአብሔር እና ፍቅር በውስጣችሁ ይኖራሉ

L

KJV መጽሐፍ ቅዱስ
ቅዱስ ሉቃስ ምዕራፍ 17 ቁጥር 21! እነሆ እዚ ፣ ወይም፣ እነሆ እዚህ አለ! ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በውስጣችሁ ናት።

እውነት፣ እግዚአብሔር እና ፍቅር በውስጣችሁ ይኖራሉ | Truth, God, and Love abide inside you

የተወደደው ኢየሱስ | Beloved Jesus
እ ኤ አ ጥር 3 ቀን 2009 ዓ.ም የተላለፈ መልእክት

ኢየሱስ ነኝ (I AM Jesus) ፣ ዛሬ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ልሰጣችሁ ነው የመጣሁት ።

ዛሬ የመጣሁት ከ2000 ዓመታት በፊት ወደ አለም ያመጣሁትን ፣ ስለ እኔ እና ስለ አስተማርኩት ትምህርት ያላችሁን አንዳንድ አመለካከቶች እና እምነቶች ለማረም ነው።

በጠፈራዊ (በኮስሚክ) መለኪያዎች፣ የኔ ትምህርት ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለው በጣም አጭር ጊዜ ነው። ይሁን እንጂ፣ በብዙ ሰዎች በተደረጉ ዝንቡል ኣገላለጾች ዋናውን የትምህርቱን ስሜት በጣም ስላዛቡት፣ እኔም እንኳን ብሆን በወንጌል ውስጥ የተጻፉትን ሐረጎች ትክክለኛ ትርጉም መገመት ያስቸግረኛል።

መልእክቴ፣ ደቀመዛሙርቴ ሊረዱትና ሊመዘግቡት ከቻሉት ትርጓሜ የበለጠ ሰፊ ነበር። ቀጣዮቹ አርታኢዎች (editors) ጽሑፉን ያለማቋረጥ ማዛባት ቀጠሉ። ብዙዎቹ በቅንነት ይዘቱን በተሻለ መንገድ ፣ በራሳቸው ተፈጥሮዋዊ መረዳት ለማስተላለፍ በማሰብ ነበር። ብዙዎቹ በኔ የተሰጡት የትምህርት ድንጋጌዎች ደግሞ ከሌሎች ሰዎች ጽንሰ-ሀሳቦች ጋር የማይስማሙ ስለነበሩ በሚስጥር ተሰርዘዋል። ለዚያም ነው ፣ምድራዊ ህይወትን ለቅቄ ከወጣሁ ከሦስት መቶ ዓመታት በኋላ፣ የተቀበላችሁት ትምህርት ፣ በእኔ የተሰጠውን እውነተኛውን ትምህርት በርቀት ብቻ ነው የሚመሳሰለው። ለማነፃፀር ያክል የሻማ እና የፀሐይን ምሳሌ ማቅረብ እችላለሁ። ያ አሁን ባለው ክርስትና ውስጥ የኔ የትምህርት መልእክት መጠን ነው ።

ቢሆንም መሰረቱ ግን ተጥሏል። እና በእኔ በኩል የተሰጠው መለኮታዊ ዕድል ፣ ለትምህርቱ ህያዊነት (ቀጣይነት) አስተዋፅኦ አድርጓል፣ በዚህም ብዙ የሚያምኑ ልቦች፣ ለብዙ መቶ ዓመታት ማረፊያ እና ሰላም መገኛ ሆኖላቸዋል። ብዙው የትምህርቱ መልካምነት የተላለፈው፣ በወንጌል ከተሰጡት ቃላቶች ይበልጥ፣ የኛን መገኘት በሞላንባቸው ምስሎቻን እና አዶውች (icons) ነበር። ስለሆነም የእኔ እና የእናቴ ማርያም ምስሎች በአዶዎች ተባዛ (ተነቃቃ)።

በምድር ላይ ፣ ብዙ አማኞች፣በምስሎቻችን አማካኝነት፣ በቀጥታ ከመገኘታችን ጋር አንድነትን በማድረግ መለኮታዊ ጸጋን በቀጥታ ይቀበሉ ነበር ።

እግዚአብሔርን ለመፈለግ ወደ ባሕታውያንና መነኮሳት መኖሪያ የሄዱት አባቶች፣ እግዜአብሄርን በልባቸው ጸጥታ ዉስጥ አግኝተዉታል። እናም የእግዚአብሄር ጸጋ፣ የጸና የመለኮታዊ ራእይ ድጋፍ ፣ በጨለመው የክረምት ምሽቶች እና ለሊቶች ጎብኝቶዋቸዋል።

የንቃተ ህሊናቸው መነቃቃት (The dawn of their consciousness) ለብዙ መቶ ዘመናት የመልእክቶቻችንን መሰረታዊ ነገሮች በሰዎች አእምሮ ውስጥ ለማቆየት አስችሏል።. እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች ፣በቀጥታ ፣ከልብ ወደ ልብ ፣ ከአባቶች ወደ እነዚያ ነፍሳቸዉን ማጽናናትን በመሻት ለቀረቡዋቸው ተላልፈዋል።

በዓለም ውስጥ ብዙ ሰዎች በልባቸው ደስተኛ አልነበሩም። እናም አሁን፣ ብዙ ሰዎች እውነተኛዉን እምነት ለማግኘት ይናፍቃሉ፣ እናም ብዙዎች እርዳታን ይፈለጋሉ።

እጅግ በጣም ያዘኑ ልቦችን ለማጽናናት እና እውነተኛ እምነት በሌለበት፣ የመጎዳት እና የመከራ ስሜትን ለማስታገስ፣ በምድር ዉስጥ ማንኛውንም ትኩረት የተሰጠበትን ነገር በመጠቀም፣ መለኮታዊ እድል ይከፈትላቸው ዘንድ ፣ በእናታችን ማርያም ፈገግታ ወይም በቤተክርስቲያን ውስጥ ባለው የሻማ ነበልባል (crackle) መገኘታችንን እናስቀምጣለን ።

ስንችል፣ ከፍተኛውን የመጽናናት ዕድል ፣ በጣም ለጓጉት እንሰጣለን። በተዛቡ ትምህርቶችም ሆነ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶች አንጨነቅም፣ በዚህ ዉስጥ የኛን እርዳታ ለሚፈልጉ ልቦች ሁሉ የእርዳታ እጃችንን ልንዘረጋ እንችላለን።

ብዙ ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣሉ፣ እኛም መጽናናትን እንሰጣቸዋለን። ሌሎች ሰዎች ከቤተክርስቲያን ባሻገር የራሳቸውን ልዩ መንገድ ይፈልጋሉ፣ እነሱንም እናጽናናቸዋለን ።

ሰዎች የትኛውንም መንገድ ቢከተሉ፣ ዋናው ነገር የልባቸው ጥራት እና የእምነታቸው ደረጃ ነው። በረሃ ውስጥ እንኳን ቢሆንም ያገኙናል።

በጣም መጥፎው ነገር ሰዎች እምነት ሲያጡ ወይም የሌሎችን መለኮታዊ ጥማት ፣ ለራሳቸው የሆነ ነገር ለመቀበል ወይም የግል ግባቸዉን ለማሳካት ሲጠቀሙበት ነው።

ወደ ምድር በመጣሁ ግዜ ፣ ስለዚያ በትክክል ተናግሬአለሁ። በከበረ አቀራረብ እና በቅዱሳን መጻህፍት  ቃላቶች ተሸፍነው፣ በጥላቻ ድርጊቶች ይሳተፉ ለነበሩ እና በምሽት እጃቸውን በደስታ ያሹ ስለነበሩት ጻፎች እና ፈሪሳውያን ግብዝነት ተናግሬ ነበር።

እኔ፣ ከሌሎች የእግዜአብሄር መልእክተኞች ጋር በመሆን፣ ሁል ጊዜም ግብዝነትን ተቃውሜያለሁ። መለኮታዊ እውነት ቀላል ነው። መለኮታዊ ፍቅር ለሁሉም ክፍት ነው። ሁሉም ነገር ግልጽ ነው፣ እናም ለመለኮታዊ ጥበብ ገንዘብን መክፈል አያስፈልግም። እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በነጻ ለሁሉም ይሰጣል።

መውጫ ከሌላቸው ፣ በሺዎች ከሚቆጠሩ መንገዶች እና አውራ ጎዳናዎች መካከል፣ ወደ መለኮታዊ ከፍታ የሚወስደዉን ጠባብ መንገድ ማግኘት ብቻ ነው ያሚያስፈልገው።

እውነተኛ እምነት ከኣምልኮ ሥርዓቶች እና በዓላት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው መገንዘብ አለባችሁ። እውነተኛ እምነት በልባችሁ ውስጥ ነው። እግዚአብሔርም በልባችሁ ዉስጥ ይኖራል። እውነተኛውን አምላክ በልባቸው ውስጥ እንዳለ ለሚገነዘቡ ሰዎች፣ ለጸሎት የሚሄዱበት የቤተ መቅደስ አይነት፣ ምንም ለውጥ አያመጣም።

ወደ ቡዲስት ፓጎዳ (Buddhist pagoda) ፣ ወደ ቤተክርስቲያን ፣ ወደ ምኩራብ (synagogue) ፣ ወደ መስጊድ ወይም ወደ ጸሎት ቤት ቢሄዱም ምንም ልዩነት የለዉም። እግዚአብሔርን ለማግኘት ወደዚያ ከሄዳችሁ፣ እግዚአብሔርን በሁሉም ቦታ ታገኙታላችሁ።.

በባዶ ልብ ወደዚያ የምትሄዱ ከሆነ ግን እግዚአብሔርን የትም አታገኙትም።

የውስጣዊ እምነት እና ቅንነት የሌለው የአምልኮ ሥርዓቶች እና ጸሎቶች ሜካኒካዊ ድግግሞሽ፣ ምንም ደግ ነገር አይሰራላችሁም። ለሺህ አመት መጸለይ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ይህን ብታደርጉም፣ ጎረቤታችሁን ለመጉዳት ከተመኛችሁ፣ ጸሎታችሁና ጥረታችሁ ኣይሰራም።

በእግዚአብሄር ስም የምትሰሩትን ወንጀል ፣ የትኛውም እምነት ሊያስተሰርየው(ሊያስተካክለው) አይችልም።

ዛሬ ቃሎቼን እንድታስቡ እጠይቃችኋለሁ። እግዚአብሔርን ለሚፈልጉ እና እሱን ለማግኘት ላልቻሉ አዝናለሁ። እናም የነሱን ልባዊ (እዉነተኛ) መነሳሳት ለብልጽግናቸው የሚያዉሉ በጣም ብዙ ሰዎች አሉ።

የእምነት ችግር መሰረቱ በልባችሁ ውስጥ ነው። በየትኛውም የአለም ሀይማኖት ውስጥ ፍጹም ታማኝ እና ቁርጠኛ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ልታገኙ ትችላላችሁ። እግዚአብሔርን እንደሚያገለግሉ በማስመሰል፣ ኢጎዋቸዉን (ራሳቸውን) ወይም ልባቸውን የያዘውን ዲያብሎስን የሚያገለግሉትን ፣ በማንኛውም ሃይማኖት ውስጥ ደግሞ ማግኘት ትችላላችሁ።

እኔ የመጣሁት ያን እውነት፣ እግዚአብሔር እና ፍቅር፣ በእናንት ዉስጥ እንጂ ፣ ከእናንተ ርቀው የሚኖሩ እንዳልሆኑ ላስታውሳችሁ ነው። በልባችሁ ዉስጥ ነው የሚኖሩት። እነዚህን ሀብቶች በልባችሁ ውስጥ ታገኙ ዘንድ እንረዳቹኅለን። እኛን እርዳታ ጠይቁን። በጥሪ እና በጸሎት ፊታችሁን ወደ እኛ መልሱ። ልባዊ ጥሪ ወደ የትኛውም ቅዱስ መልአክ (Ascended Master) ሊደርስ ይችላል፣ እናም ጥሪን መመለስ እንደ ግዴታችን ስለምንቆጥር፣ ለእናንተ ምላሽ ኣለመስጠት አይቻለንም፣ እናም ይህ ተግባር ለኛ የተቀደሰ ነው።

 ኢየሱስ ነኝ (I AM Jesus) 

ይህ ጽሁፍ በ ሲሪየስ ኔት ድህረ ገጽ ላይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የኢየሱስ መልእክት በ መልእክተኛዋ ታትያና ሚኩሺና በኩል የተላለፈዉን ቃል በቃል ተተርጉሞ የቀረበ የአማርኛ ትርጉም ነው። This article is a verbatim translation of the english version of the Lord Jesus message as it has been received by the Messenger Tatyana Mickushina. The message was streamed on January 3, 2009, on the following website:- follow this link

ተርጓሚ መስፍን ሃጎስ ተወልደ (ዕለት :- እ ኤ አ 24.10.2021)