KJV መጽሐፍ ቅዱስ
ቅዱስ ሉቃስ ምዕራፍ 17 ቁጥር 21! እነሆ እዚ ፣ ወይም፣ እነሆ እዚህ አለ! ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በውስጣችሁ ናት።
እናታችን ማርያም | Mother Mary እ ኤ አ ጥር 4 ቀን 2009 ዓ.ም የተላለፈ መልእክት
I AM Mother Mary/ እናታቹህ ማርያም ነኝ፣ እንደተለመደው ልብ ለልብ ለመነጋገር ወደናንተ መጥቻለሁ። ልቦች ሲያወሩ ኣእምሮዎች ዝም ይላሉ እናም በመካከላችን እዉነተኛው ኣንድነት የሚኖረው የልብ ለልብ አንድነት ስንመሰርት ብቻ ነው።
ፍቅር ካጣችሁ ፣ ብርሃንም ከሌላችሁ። ከመለኮታዊ ኃይል (ከእግዚአብሔር ኃይል) ማነስ የተነሳ፣ የኦክስጂን እጥረት ያለ እስኪመስላችሁ ድረስ ፣ አንዳንድ ጊዜ በከፊል ትንፋሽ ያጥራችሁዋል። በዚህን ጊዜ ከእኔ ጋር ልብ ለልብ በመነጋገር የበዛ ጊዜ ማሳለፍ አለባችሁ።
ሁሉንም ችግሮቻችሁን እና ጸሎታችሁን ለማዳመጥ ዝግጁ ነኝ። ፍርሃት ኣይሰማችሁ። በተለይ ወንዶች የሚሰማቸዉን ለመግለጽ ያሚያፍሩ እንደሆኑ አውቃለሁ። በጸሎት ጊዜ ያ ልዩ ያንድነት ጊዜ ሲደርስ ፣ ግራ በመጋባት በዓይኖቻቸው ላይ የሚወጣውን እንባ ይጠርጋሉ።
ለማልቀስ ነፃ ሁኑ። ነፍሳቹህ እውነተኛውን ኣንድነት ትናፍቃለች። ወንዶችም ሆናችሁ ሴቶች ፣ በአለም ውስጥ ፍጹምነትን ብትፈልጉትም ኣላገኛችሁትም። በአካላቹህ (በገላችሁ) ላይ ታተኩራላችሁ፣ ነገር ግን እውነተኛ ፍቅር እራሱን የሚገልጠው በነፍሳችሁ ደረጃ እና ከመለኮታዊ ምንጭ ጋር በተዋሃሃደው በ እዉነተኛው የናንተ አካል (your Higher Self ) ነው።
በጸሎት አንድነታችን ጊዜ ፣ ዓይኖቻችሁ በእንባ ቢሞሉም አትፍሩ። ባለፈው የሕይወት ዘመናቹህ እናም በዚህ የሕይወት ዘመናቹህ ውስጥ፣ በሴቶች፣ በእናቶች እንዲሁም በእህቶቻችሁ ላይ ደግ ያልሆነ ነገር ብዙ ግዜ ፈጽማቹኅል። ያ ደግ ያልሆነ ስራ በእንባችሁ ውስጥ ይሟሟ ፣እና ያም የህይወት ሸክም (negative energies) እስከ ዘላለሙ ይራገፍ። የናንተ ንስሃ ፣ ምንም እንኳን ንስሃ መሆኑን ባታስተውሉትም ፣ አዲስ ዕድል ይከፍትላቹሃል፣ ኣዲስ የዓለም እይታ ።
ስለ እንባችሁ ኣትፈሩ። ባለማወቃችሁ ወይም ከጥበብ ማነስ የተነሳ የፈጠራችሁትን የሃጢያት ጥርቅም ምላሽ (ካርማ) ጠርጎ ይወስድላቹሃል። እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ። እኔ ሁል ጊዜም ቢሆን ከእናንተ ጋር አለሁ ፣ እና ሁልጊዜም ቢሆን በችግራችሁ ግዜ ለእርዳታ ፊታችሁን ወደ እኔ መመለስ ትችላላቹህ። በልዩ ተልዕኮዬ ምክንያት ፣እኔ ከሁሉም ቅዱሳን (Ascended Masters) በይበልጥ ለምድር (ለመሬት) ቅርብ ነኝ።
ቤታችሁን እና ሀገራችሁን እጠብቃለሁ። ለጥረታችሁ እንዲሁም ለምትልኩልኝ ያ የፍቅር እና የጸሎት ኃይል ምስጋና ይግባዉና፣ በመጀመሪያ ግዜ በምታደርጉት ጸሎት ወደናንተ ለመምጣት ዝግጁ ነኝ። ለኔ ብላችሁ ምታደርጉት የዉዳሴ ጸሎት ፣ እርዳታዬን ለሚሹ ሁሉ እርዳታ እንዳደርስ ዕድል ይሰጠኛል።
ከልባችሁ የዉዳሴ ጸሎት በምታደርሱበት ጊዜ ይታወቀኛል ። የኃይል ዥረት በመካከላችን ይፈስሳል፣ከእናንተ ወደ ላይ እና ከእኔ ደሞ ወደ ታች። በዚህ አይነት መንገድ ነው የፍቅር እና የምህረት ኃይሌ ወደናንተ የሚደርሰው። በተለይ ባዘናችሁበት ወቅት እና ዉዳሴ ማሪያምን ለመድገም ምንም ኃይል በማይኖራችሁ ጊዜ ፣ ስለእኔ ማሰብ ትችላላችሁ፣ በስሜ የተዜሙ ዜማዎችንም አዳምጡ፣ በዚህ ጊዜ ከእናንተ የሚፈሰው ኃይል ወደ እኔም ይደርሳል ፣ እናም ሁላችሁንም እሰማለሁ ። በእግዚአብሔር ቸርነት ፣ የእግዚአብሄር ልጆች ስለ እኔ በሚያስቡበት ወቅት ወይም ለእርዳታ ፊታቸዉን ወደ እኔ ሲመልሱ ይሰማኛል። ስለዚህ ዛሬም እንደበፊቱ በሰማይ የተሰጣችሁን ዕድል ተጠቅማችሁ ፣ እርዳታ በምትፈልጉበት ጊዜ ድጋፌን እንድሰጣችሁ ጠይቁኝ።
ውድ እየሱስ ትላንትና እንደነገራቹህ፣ በብዙ ምስሎቼ ላይ መገኘቴን (my presence) ኣድርጌያለሁ። እናም እራሳችሁ ልትገነዘቡት (feel) ወይም ሊሰማችሁ ይችላል። ኣንዳንድ የኔ አዶዎች (icons) ተአምራትን ያደርጋሉ። እናም አንዳንድ ጊዜ፣ የኔን የምህረት ጨረር ለመቀበል፣ ከአዶዎች አንዱን ማየት ብቻ ይበቃችሁዋል።
በመካከላችሁ ለመገኘት እድሉ ሲኖረኝ ፣ መገኘት መቻሌ የእግዚአብሔር ቸርነት ስለመሆኑ ምስጢር አደለም፣ በአጠገባችሁ መኖሬን ላታስተዉሉት ትችላላቹ እንጂ ባላችሁበት ቦታ ለመገኘት እችላለሁ። ለእኔ በጣም አስፈላጊዉ ነገር እናንተ በሰላም ድባብና ጸጥታ ባለው ሁኔታ መቆየት አለባችሁ። በማይታይ ሁኔታና በማይታወቅ ሁኔታ እመጣለሁ፣ እናም አጠገባችሁ በተገኘሁ ጊዜ፣ አልፎ አልፎ ከኔጋር አብሮ በሚኖረው ትንሽ የሮዝ መዓዛ አማካኝነት እንደጎበኘዋቹህ መገመት ትችላላቹ።
በዚህ የክረምት ቀን ዜና ይዤ መጥቻለሁ ፣ ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ። በጸሎት ጊዜያችሁ እጅግ ቅድስት ለሆነችው ለእግዚአብሔር እናት የምትጸልዩበት ጸሎት ልሰጣችሁ እወዳለሁ።
“በ “ኣይ ዓም ዛት ኣይ ዓም“ ስም (In the name of I AM THAT I AM) ፣ እጅግ ቅዱስ የእግዚአብሔር እናት ፣ የተወደድሽው እናታችን ማርያም ፣ተንበርክኬ ወደኣንቺ እጸልያለሁ። ላንቺ ስላለኝ የጠለቀ መዉደድ በቃላቶች ሊገለጽ አይቻልም።እባክሽን ፍቅሬን እና ምስጋናዬን ተቀበይው። በዚህ ጊዜ ለነፍሴ እድገት በጣም አስፈላጊ የሆነውን፣ ኣንቺ ታዉቂያለሽና።እርዳታሽ እና ድጋፍሽ እንዳይለየኝ እፀልያለሁ።የጸሎት አንድነት ባደረግንባቸው ጊዜያት፣ነብሴ የምታስታዉሰዉን ፣ በዉኔ ሆኜ እንዳልረሳው ትደግፊኝ ዘንድ እፀልያለሁ። ከኣንቺ ጋር ያለኝ የማይሰበር አንድነት፣ በዚህኛው ህይወቴ ዉስጥ ልከተለው የሚገባዉን የቅዱሳን መንገድ (Higher Path) ፣ እንዳልረሳ ይደግፈኝ ፣ እንዲሁም ይርዳኝ።”
በመደጋገም ከኔ ጋር ሆናችሁ በጸሎት እንደምታሳልፉ ከልቤ ተስፋ አደርጋለሁ። ማንኛቸውም የጸሎት ጊዜያችን ፣ ወይም የኔን ምስል መመልከት የንቃተ ህሊናችሁን ወይም የንዝረታችሁን መጠን ከፍ አርጎ ስለሚያቆይላችሁ፣ እስካሁን ወደ ልቤ መንገዱን ያላገኙት እና የሚያደርጉትን የማያውቁ ሰዎች ጥቃት ሊያደርሱባችሁ አይቻላቸዉም።
I AM Mother Mary/ እናታቹህ ማርያም ነኝ፣ በዚህ ቀን ከእናንተ ጋር ነበርኩ።
ይህ ጽሁፍ በ ሲሪየስ ኔት ድህረ ገጽ ላይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ እናታችን ማሪያም በ መልእክተኛዋ ታትያና ሚኩሺና በኩል ያስተላለፈችዉን መልእክት ቃል በቃል ተተርጉሞ የቀረበ የአማርኛ ትርጉም ነው። This article is a verbatim translation of the english version of the Mother Mary message as it has been received by the Messenger Tatyana Mickushina. The message was streamed on January 4, 2009, on the following website:- follow this link
ተርጓሚ መስፍን ሃጎስ ተወልደ (ዕለት :- እ ኤ አ 20.10.2021)