Birhan | Spiritual Messages, Teachings & Insights.

Birhan Logo: A stylized representation of the company's name, with vibrant colors and modern design.

መልዕክት ለምድር ሰው

L

KJV መጽሐፍ ቅዱስ
ቅዱስ ሉቃስ ምዕራፍ 17 ቁጥር 21! እነሆ እዚ ፣ ወይም፣ እነሆ እዚህ አለ! ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በውስጣችሁ ናት።

መልእክት ለምድር ሰው | A Message to Mankind of Earth

የተወደደው አልፋ ( የሰማዩ ኣባታችን) | Beloved ALPHA (Our Heavenly Father)

እ ኤ አ ሰኔ 1 ቀን 2005 ዓ.ም የተላለፈ መልእክት

አልፋ ነኝ (I AM Alpha) ፣ በምድር ለሚኖሩ ለሰው ልጆች (ሰብአዊ ፍጡር) ሁሉ መልእክት ይዤ መጥጫለሁ ።

(I AM) እኔ ነኝ፣ በዚህ ወቅት የትኩረት ስህበታችሁን አቅጣጫ መጠበቅ የሚያስችላችሁን ጠቃሚ መልእክት ለመስጠት መጥቻለሁ። በልባችሁ ላይ አተኩሩ – ልባችሁ እና እናንተ ብቻ ፣ ዉድ ልጆቼ ሆይ።

ሌላ ምንም በዚህ ዓለም ዉስጥ የለም። ወደ መለኮታዊው እውነት የሚያሻግራችሁ ብቸኛው መግቢያ ፣ በልባችሁ ዉስጥ ይገኛል።

በጉዑዙ ዓለም (physical world) ውስጥ ፣ በዙሪያችሁ ያሉ ነገሮች ሁሉ፣ ለመበልጸግ እና ለማደግ ፣ እራሳችሁን ለማሸነፍ እና ንቃተ ህሊናችሁን ለማጎልበት እንዲሁም ለእድገታችሁ የሚያግዝ ብቻ ነው።

እናንተ ያለማቋረጥ በእንቅስቃሴ ላይ የምትገኙ ተጓዦች ናችሁ። በማትንቀሳቀሱበት ግዜ እንኳን፣ ከፕላኔታችሁ ፣ ከፀሀይ ስርአታችሁ (solar system) እና ከጋላክሲያችሁ (Galaxy) ጋር በመሆን በሺዎች እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመብረር፣ በአለማችሁ ዉስጥ ሰፊ ርቀት ትጓዛላችሁ ።

ይህ ውጫዊው አጽናፈ ሰማይ (ዩኒቨርስ) ነው። እና ሌላ አጽናፈ ሰማይ (ዩኒቨርስ) አለ፣ ውስጣዊ ዩኒቨርስ ፣ እናም የዚህ አጽናፈ ሰማይ (ዩኒቨርስ) መግቢያ በር በውስጣችሁ፣ በልባችሁ ውስጥ ይገኛል።

ቀጣዩ እርምጃችሁ መሆን የሚገባው ይህን ወደ ሌላ ዓለም መግቢያ በር የሆነዉን ማግኘት ነው፣ መለኮታዊው ዓለም – ዘላለማዊው (timeless ) እና ጠፈር (ህዋ) የለሹ፣ ሁሉም ነገር የሚቻለው እና ፍፁም የሆነ ዓለም፣ የሁሉም ነገር ምንጭ እና የሁሉም ነገር መመለሻ የሆነው ዓለም። ይህ ዓለም የናንተ ዓለም ነው ፣ የናንተው ቤት፣ የናንተ እዉነተኛ መገለጫ። ከዚሁ ዓለም ነው ፣ወደ ግዑዙ ዓለም (physical world ) መጥታችሁ ቁሳዊዉን ዓለማችሁን (material world) የፈጠራችሁት ።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍጥረተ ብርሃን (Biengs of light) ግዑዙን ዓለም (የዉጨኛዉን ዓለም) በመፍጠር ላይ ነበሩ እናም አሁንም እየፈጠሩ ነው። እናንተም ፣እያወቃችሁት ወይም ሳታውቁትም ቢሆን ፣ እያንዳንዳችሁ በዚህ በዉጨኛው ዓለም የፈጠራ ሂደት ዉስጥ እየተሳተፋችሁ ነው። አንድ ህጻን ልጅ፣ የዓለምን መዋቅር እና ውስብስብነቱን ላያስተውለው ይችላል፣ ነገር ግን እሱም በዚሁ ግዑዙ ዓለም ውስጥ ተወልዶ ይኖራል።

ከዚያም ህፃኑ ያድጋል፣ እውቀትን ያገኛል እና በዓለም ግንባታ እና በእንቅስቃሴው ውስጥ በንቃት ይሳተፋል።

እናንተ ልጆች ናችሁ። በእናንተ ንቃተ ህሊና ደረጃ፣ ዓለማትን መፍጠር እናም የእነዚህን ዓለማት ሥርዓት እና ንጽሕና ለመጠበቅ በንቃት መሳተፍ አትችሉም። ነገር ግን አሁን ጊዜው ደርሷል ፣ ስለዚህ ማደግ አለባችሁ ።

ወደ አዋቂዎች ዓለም ለመግባት፣ የመጨረሻው ፈተናችሁ የሚሆነው፣ ወደ ልባችሁ የሚያስገባዉን በር መፈለግ ነው፣ ወደ እውነተኛው የእግዚአብሔር ዓለም መግቢያ በርን ማግኘት ነው።

እነዚህን መልእክቶቼን እያነበባችሁ ያላችሁ በሙሉ፣ የመጨረሻውን ፈተናችሁን ልታልፉ እንደምትችሉ በእውነት ተስፋ አደርጋለሁ፣ ይህ ፈተናም፣ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ፈጣሪ የመሆን እና፣ በዚህ አጽናፈ ዓለም (ዩኒቨርስ) ዉስጥ፣ የእግዚአብሔርን እቅድ አውቃችሁ፣ ወደ ህይወት የመተግበር ስልጣን ለናንተ ይሰጣችሁዋል። በልባችሁ ዉስጥ ተሸፍኖ በሚገኘው ሚስጥራዊው ስፍራ ባለው ፣ በጠባቡ ሚስጥራዊ በር ማለፍ አለባችሁ።

ከእናንተ ዉጪ ላሉ የሩቅ ዓለማት እዉቀት ይኖራችሁ ዘንድ፣ ማንም ወደ እሩቅና አስደናቂ የጠፈር ጉዞ እንኳን ቢጠሯችሁ፣ አትመኑዋቸው። የሁሉም ዓለማት፣ የሩቅ እና የሌሎች ዓለማት መግቢያ በር፣ በልባችሁ ውስጥ ነው ያለው። በልባችሁ ውስጥ ያለው በር ቁልፉ ፍቅር ነው።

እናም ይህንን በር በንቃተ ህሊናችሁ (በንቃተ አእምሮዋቹህ) እርዳታ ነው የምትከፍቱት፣ በመለኮታዊ ንቃተ ህሊናችሁ።

ውጫዊው (አለማዊው) ንቃተ ህሊናችሁ (your external conciousness) እና ውጫዊው አእምሮዋቹህ (your external mind) እንቅፋት ይሆኑባችሁዋል፣ እና በመንገዳችሁ ላይ መሰናክሎችን ደግመው ደጋግመው ያስቀምጣሉ።

አሁን ግን፣ ወደ ዓለም የሚያስገባው የሚስጥር በር፣ የት እንዳለ፣ ከየት እንደመጣችሁ እና ወዴትም እንደምትመለሱ፣ አውቃቹሃል። በህይወት ፈተናዎቻችሁ ወቅት የዚህን በር ቁልፍ ለማስታወስ ሞክሩ። እናም በዚህ ጠባብ በር ውስጥ እንዳትገቡ የሚከለክሉትን ሁሉንም ነገሮች፣ ከንቃተ ህሊናችሁ ለማስወገድ ሞክሩ።

በጠፈር (space) እና በጊዜ ውስጥ በምትጓዙበት ወቅት ካገኛችኃቸው እና አሁንም ከምታገኟቸው የማይናቁ ልምዶች በስተቀር ፣ በዓለም ውስጥ ካሉት ነገሮች አንዱም ነገር ፣ በእውነተኛው የእግዚአብሔር ዓለም ዉስጥ የሚጠቅማችሁ ነገር የለም።

እና ስለምን ወደ እናንተ ዓለም እንደላኳችሁ ትዝ ቢላችሁ – ዉዱን ሀብት (treasure) እንድታገኙ ነው የላኳቹህ። እና ይህ ውድ ሀብት የእናንተ ምክንያታዊው አካላቹህ (Causal Body, an imperishable part of you) ነው። ይህ ትልቁ ሃብት፣ በዋጋ ሊተመን የማይችል ውድ ሀብት ነው – ዝገትም ሆነ ብል የማያሰጋው ሀብታችሁ።

ብዙዎቻችሁ ሀብታችሁን አግኝታችኋል፤ ስለዚሁ ነው ወደ ዓለም የላክኋችሁ። እና አሁን ማንነታችሁን እና ለምን ወደ ዛ ዓለም ለመጓዝ እንደወሰናችሁ ታስታዉሱ ዘንድ ፣ ወደ ቤት መመለስ አለባችሁ።

ለመለኮታዊው እውነት (Higher Reality) የመንቃት ጊዜው አሁን ነው። ዘመኑ ተገባዷል ስለዚህም ጊዜው ደርሷል። መንገዱን አሳይተናቹኃል። መንገዱን ታውቁታላችሁ። ወደ ቤት ለመመለስ የሚያስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ አላችሁ። ልጆቼ እየጠራኋችሁ ነው።

ስለእናንተ ብዙ አስባለሁ። (I miss you ) ። እያዳመጣችሁኝ ነው?

ስለዚህ ማንኛችሁም ብትሆኑ፣ በህይወት ዘመን ጉዟችሁ ዉስጥ፣ይህን ዉድ ሀብት (treasure) ያላገኛቹሁት ከሆነ፣ ተስፋ አትቁረጡ። ባዷችሁን ብትመጡም እንኳን በደስታ እቀበላችኋለሁ ። ወደ ቤታችሁ (to your heavenly home) ብቻ ተመለሱ። በልባችሁ ዉስጥ ያለዉን ሚስጥራዊውን በር ፈልጉ።

እየጠበቅኳችሁ ነው፣ የኔ ልጆች።

I AM ALPHA/ የሰማዩ አባታችሁ አልፋ ነኝ።

ይህ ጽሁፍ በ ሲሪየስ ኔት ድህረ ገጽ ላይ በእንግሊዘኛ ቋንቋ በመልእክተኛዋ ታትያና ሚኩሺና በኩል የተላለፈዉን የእግዜአብሄር መልእክት ቃል በቃል ተተርጉሞ የቀረበ የአማርኛ ትርጉም ነው። This article is a verbatim translation of the English version of the Lord Alpha (Our Heavenly Father) message as it has been received by the Messenger Tatyana Mickushina. The message was streamed on Jun 1, 2005, on the following website:- follow this link

ተርጓሚ መስፍን ሃጎስ ተወልደ (ዕለት :- እ ኤ አ 26.10.2021)