Saint Germain| ቅዱስ ጀርሜን

ቅዱስ ጀርሜን በዚህ ወቅት ወደ ሰማይ ያረገ ማስተር (መምህር) ና የአዲሱ ዘመን ተዋረድ ኣባል ነው።  በ መጨረሻው የምድር ላይ ህይወቱ በ 18 ኛው ምእተ ኣመት እንደ  መኳንንት ቅዱስ ጀርሜን ተወልዶ በነበረበት ግዜ፣  በዓለም ታሪክ ሂደት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

የ 18ኛው ክፍለ ዘመን በጣም ሚስጥራዊው ሰው።

አብዛኛዎቹ የሕይወት ታሪክ ጸሐፊዎቹ እና ተመራማሪዎቹ ቅዱስ ጀርሜን ከሃንጋሪ ንጉሣዊ ቤት ከራጎዚይ (Ragoczy) ቤት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደነበረው በአስተያየታቸው ይስማማሉ።

በቅዱስ ጀርሜን ዘመን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ሲገልጹት፣ የመካከለኛ ቁመት እና የተመጣጠነ የሰዉነት ቅርጽ እንዳለዉና ፣ እንደማንኛዉም የዘመኑ ሰው መደበኛ ባህሪያዊ ቅርጽ  እንደ ነበረው ይናገራሉ።  የዓይኖቹን ዉስጥ ላየ ሰው ፣ በኣመለካከቱ ይማረኩ ነበረ።

አንዲት የኣድሀማ (d’Adhémar) መኩዋንንት ባለቤት (እመቤት)፣በፈረንሣይ ፍርድ ቤት፣  ቅዱስ ጀርሜንና ፣ ስለ ነበረው ገጽታ የገለጸችበት መንገድ ይህ ነው  “እ.ኤ.አ በ 1743 ነበር፣ ከጌጣጌጡ ግርማ ሞገስ በመነሳት፣ እጅግ በጣም ሀብታም የሆነ እንግዳ ወደ ፈረንሳይዋ ከተማ ቨርሳይ (Versailles) ደርሷል የሚል ወሬ የተሰማው። ከየት መጣ?  ማንም ሰው ሊያዉቀው ያልቻለው ይህንኑ ነው። ከእሱ ጋር ለተወያየ፣ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ፣  ችሎታዉና  ብልህነቱ ያስደምመዋል። ገላጭና ፣ ግርማ ሞገስ ያለው ፣ ለስላሳ እጆች ፣ ኣነስ ያሉ  እግሮች ነበረው። ፈገግታው በጣም የሚያምሩ ጥርሶችን ብልጭ ያረጋሉ ፣ ቆንጆ የሰረጎዱ ጉንጩቹ አገጩን ያስጌጡታል። ጸጉሩ ጥቁር ፣ ዓይኖቹ ለስላሳ እና ዘልቆ የሚገባ ነበር። ኦ! በጣም ቆንጆ አይኖች! እኔ እንዲህ የመሰለ ዓይን  የትም አላየሁም። ከአርባ እስከ አርባ አምስት ዓመት መካከል ያለ ሰው ይመስላል። ”

ሌላ በሱ ዘመን የነበረ ሰው፣ ቅዱስ ጀርሜንን በሚከተሉት ቃላት ገልጾታል  “ቅዱስ ጀርሜን መካከለኛ ቁመት እና የሚያምር ኣለባበስ ያለው ሰው ነው። ገጽታው ልሙድ ሆኖ፣ ፀጉሩ ጥቁር፣ ፊቱ በዉበትና በእዉቀት የተሞላ፣ ቅርጸ ኣካላቱ ሞገስ የነበረው፣ ከመኳንንቶች ዝርያ ያለው የሚመስል ነበር። የመኳንንቱ አለባበሶች ቀላልና ማራኪ ነበሩ። ልብሶቹ በብዙ አልማዞች የተሽቆጠቆጡ ናቸው። በእያንዳንዱ ጣት ላይ ኣልማዝ ያጠልቃል፣ እንዲሁም  በአልማዝ ማኖሪያ ሳጥኖቹ እና ሰዓቶቹ ውስጥም እንቁ ይታያል። አንድ ቀን፣ ከሰዓት በኋላ  በእንቁ የተሸፈነ የጫማ ቁልፍ ኣጥልቆ ወደ ፍርድ ቤት ቀረበ ። ስለዚህ እንቁ ፣ የከበሩ ድንጋዮች ባለሙያ የሆኑት ሄር ቪ.ጎንቶ (Herr V. Gontaut) እንደገመቱት፣ ወደ 200, 000 ፍራንክ (የፈረንሳይ ገንዘብ) ይደርሳል።

መኳንንቱ ቅዱስ ጀርሜን የ 18ኛው ክፍለ ዘመን በጣም ሚስጥራዊ ሰው ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ይህም ምስጢር በሁሉም ነገር ይገለጥ ነበር። በሚስጥር ስለተሞላው ህይወቱና ያለተረጋገጠ ዕድሜው፣ ከሁሉም ነገሥታት እና በርካታ የአውሮፓ እና የእስያ የፖለቲካ ሰዎች ጋር በቀጥታ በመተዋወቁ እና በመገናኘቱ ፣ በዚያን ጊዜ ከነበሩት በርካታ ዋና ዋና የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ በመሳተፉ ፣ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴዎቹ እና ብዙ ተሰጥዖቹ ፣ ሳይንሳዊ ጥናቶቹ እና ቴክኒካዊ ፈጠራዎቹ ፣ የቅመማ ሙከራዎቹ ፣ የፈውስ እና ሳይኪክ ችሎታው ፣ ስለ መንፈሳዊ ጥልቅ እዉቀቱ ይወራ ነበር።

የተወለደበት እና የሞተበት ቀናትም በምስጢር የተሸፈነ ነው። መኳንንቱ ያረጀ አይመስልም። ኢዛቤል ኩፐር-ኦክሌይ (Isabel Cooper-Oakley) እ.ኤ.አ በ 1911 በተፃፈው መጽሐፏ ውስጥ “The Comte de Saint Germain. The Secret of Kings (መኳንንት ቅዱስ ጀርሜን፣. የነገሥታት ምስጢር) ” መኳንንቱን ስላዩት ሰዎች ምስክርነት ጽፋለች። ይህ ማስረጃ የተሰጠው እ.ኤ.አ ከ 1710  እስከ 1822  ባለው ጊዜ ይሆናል ( እንግዲህ ተመልከት እ.ኤ.አ  በ 1710 ይህ ምስጢራዊ ሰው የ 45 ዓመት ጎልማሳ ይመስል ነበር)።

የቀደመው የታሪኩ መዝገብ እንደሚገልጸው “ከሃምሳ ዓመታት በፊት ከባለቤቷ ጋር ወደ ቬኒስ የተጓዘችው አሮጊቷ እመቤት ቪ. ጆርጅይ (V. Georgy) ወደ መኳንንቱ ቀረበችና እንዲህ ስትል ጠየቀችው “አባትህ እ.ኤ.አ በ 1710 ገደማ በቬኒስ ውስጥ ይኖር ነበርን?”።

መኳንንቱ ግድ በሌለው ስሜት እንዲህ ሲል መለሰ “አይ እመቤቴ ” ፣  “አባቴ ከረጅም ጊዜ በፊት ነው የሞተው። ግን እኔ ራሴ ባለፈው ክፍለ ዘመን መጨረሻ እና በዚህ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በቬኒስ ውስጥ እኖር ነበር። ያን ጊዜ ካንቺጋ አብሬ በመስራቴ ክብር ይሰማኝ ነበር ፣ እናም አብረን የምናቀነቅነዉ ከነበረው ጥቂቶቹን የሙዚቃዎቼን ቅኝት የምታደንቂ ሰው ነበርሽ።

ይቅታ ኣድርግልኝና ያ የማይቻል ነው። በዚያን ጊዜ የማውቀው መኳንንቱ ቅዱስ ጀርሜን ቢያንስ 45 ዓመቱ ነበር ፣ እና አሁንም በግምት ያንኑ ዕድሜ ነው ያለህ ማለት ይቻላል።

መኳንንቱም በፈገግታ “እመቤቴ ፣ እኔ ዕድሜዬ በጣም ብዙ ነው” ሲል መለሰ።

እና ታዲያ 100 ዓመት ገደማ ሆኖሃል? “ይህ ደሞ የማይሆን ነው።”

ከላይ የተጠቀሰችው የኣደህማ እመቤት (Countess d’Adhémar) ከቅዱስ ጀርሜን ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘችበትን ቀን በማስታወሻ ደብተሯ ውስጥ “በዱክ ደ ቤሪ (Duke de Berri) ግድያ ዋዜማ [1820]” ተመዝግቧል።   እናም ቅዱስ ጀርሜን  በመጀመሪያ ትዉውቃቸው  ላይ  ካየችው ምንም ኣልተለወጠም ነበር ።

የመኳንንቱ ዕውቀት በዓለም ላይ ባለው ነገር ሁሉ ላይ ይገለጻል

 

ቅዱስ ጀርሜን ብዙ ቋንቋዎችን ይናገር ነበር። እሱም  ቋንቋውን በትክክል ከመናገሩ የተነሳ ቋንቋዉን የሚነገርበትን ሃገር ተወላጅ ይመስል ነበር። የእነዚህ ቋንቋዎች ብዛት ፈረንሳይኛ ፣ እንግሊዝኛ ፣ ጀርመንኛ ፣ ጣልያንኛ ፣ ስፓኒሽ ፣ ፖርቱጋልኛ ፣ ሩሲያኛ ፣ ሳንስክሪት ፣ ግሪክኛ ፣ ቻይንኛ ፣ አረብኛ እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ታሪክን ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበር በሚተርካቸው ክስተቶች ውስጥ የተሳተፈ ይመስላል።

መኳንንቱ ጎበዝ ሙዚቀኛ ነበር እናም ያለ ሙዚቃ ኖት ቫዮሊን እና ፒያኖን በጥሩ ሁኔታ መጫወት ይችል ነበር። እሱ የተጫወታቸው የሙዚቃ ቅንብሮች የፍቅር ብቻ ሳይሆኑ በጣም የተወሳሰቡ ኮንሰርቾችንም ያካትት ነበር።

መኳንንቱ እንዲሁ ጥሩ የዘይት ቀለም ሰዓሊ ነበር። እሱ የፈጠራቸው ስእሎች እጅግ በጣም ልዩ ነጸብራቅ ያፈነጥቃሉ። እሱ የሳላቸው  ሰዎች አልባሳት እንደ ዕንቁዎች የሚያብረቀርቁ ይመስላሉ።

ቅዱስ ጀርሜን በሕክምና እና በዕፅዋት መድኃኒት  አጠቃቀም ረገድ የተካነ ነበር። አንዳንድ የሱ ዘመን ሰዎች እንደሚሉት እሱ የፈለሰፋቸው መድኃኒቶች ና ቀለል ያለ የምግብ የመመገብ ልማዱ ፣ የመኳንንቱን  ጤና ገንብቶ ዕድሜውን እንዳራዘመ ያስቡ ነበር።

መኩዋንንቱ  እ.ኤ.አ ከ 1737  እስከ 1742  በነበረበት፣ በፋርስ ሻህ ፍርድ ቤት በሳይንሳዊ ምርምር ውስጥ ተሰማርቶ የከበሩ ድንጋዮችን ፣ በተለይም የአልማዞችን ጥራት ውይም ብሩህነት በመጨመር  ችሎታውን አሳይቷል።

መኳንንቱ  በተለያዩ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስኮች ብዙ ግኝቶችን አድርጓል።

በግራፍ ካርል ኮበንዝል (Graf Karl Cobenzl) ምስክርነት መሠረት ፣ ቅዱስ ጀርሜን የጅምላ ማምረቻ ቴክኒኮችን እያዳበረ ነበር። ለምሳሌ ፣  ከልዩ ልዩ ተልባ እግርና ጭረት ጠጉር ጥጥ የሚሠራ ሱፍ ልብስን የማንጣት (ሱፍ ልብስን  ማቧጨት)  ዘዴው ጨርቁን የጣሊያን ሐር እንዲመስል አድርጎታል ፣ እና ደግሞ  እጅግ በጣም ፍጹም የቆዳ ኣዘገጃጀት ዘይቤው በዓለም ላይ ካለው ምርጥ የሞሮኮ ቆዳ በልጧል። ቅዱስ ጀርሜን እስካሁን ያልታወቀ ፍጹምነት የተሸለመዉን የሐር እና የሱፍ ጨርቅ የቀለም አነካከር ዘዴ ፈልስፎዋል። በተለመዱት ንጥረ ነገሮች  ኣዝልቆ የመግባት ዘዴን በመተግበር በተመጣጣኝ  ዋጋ እንጨቶችን ወይም ጣዉላዎችን እጅግ በጣም በሚያንፀባርቁ ቀለሞች መቀባትን ፈልስፎዋል ።

በቅዱስ ጀርሜን  የቀረቡት ብዙ ፈጠራዎች ከረዥም ጊዜ ጀምሮ የሰው ልጅ ሥልጣኔ የጋራ ንብረት ሆነዋል። ቢሆንም ፣ አንዳንዶቹ አሁንም ከእኛ ምናብ በላይ ናቸው። ለምሳሌ ፣ ግራፍ ማክሲሚሊያን ጆሴፍ ቮን ላምበርግ (Graf Maximilian Joseph von Lamberg) እ.ኤ.አ በ 1775 ቅዱስ ጀርሜን የተፈጠረውን የ ፈትል  ማሽከርከሪያ (ማጦዢያ)፣ በአንድ ጊዜ ሁለት ፈትል (ክርዎችን) ያመረተ መሆኑን ጽፎዋል ፣ ግን ይህ ዘዴ የሠራተኛውን የኣትኩሮት መከፋፈልና በአንድ ጊዜ ሁለቱንም መቆጣጠርን ይጠይቃል። ግራፍ ቮን ላምበርግ (Graf von Lamberg) በወቅቱ ሰዎች በንቃተ ህሊና እና በችሎታቸው ማነስ ምክንያት ይህንን ዘዴ መጠቀም አለመቻላቸውን በሐዘኔታ ገልፀዋል። ይህ ምሳሌ በግልጽ እንደሚያስቀምጠው በወቅቱ በቴክኖሎጂ አብዮት መባቻ ላይ፣ ቅዱስ ጀርሜን በሰው ልጅ ውስጣዊ ችሎታዎች እድገት ላይ መሰረት መጣሉን በጥልቀት ያስረዳል።

ሉዊ 15ኛው የቅዱስ ጀርሜንን የኣልቼሚይ (alchemy) ችሎታን ከፍ አድርጎ በመመልከት በንጉሣዊው ቻቶ ዴ ቻምበርድ (Château de Chambord) ውስጥ ላቦራቶሪ እና የራሱ ክፍሎች እንዲመደብለት አድርጎዋል። በዘመኑ የነበሩት ምስክር እንደሰጡት ፣ የቅዱስ ጀርሜን የ አልቼሚይ (alchemy) ክፍለ ጊዜ ተዓምራት የሚታይበት እንደነበር ገልጸዋል።

የቅዱስ ጀርሜን ጂኦግራፊያዊ ጉዞዎች አውሮፓን ፣ እስያን እና አፍሪካን ይሸፍናል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በአሜሪካ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው። ማዳም ዴ ፖምፓዶር (Madame de Pompadour) እንደጻፈችው፣ ቅዱስ ጀርሜን በዓለም ዙሪያ እንደተዘዋወረ እና ንጉሱ በእስያ እና በአፍሪካ ስላደረጋቸው ጉዞዎች እና እንዲሁም ስለ ሩሲያ ፣ ቱርክ እና ኦስትሪያ ፍርድ ቤቶች ትዝታዎቹን በፀጋ አዳምጦታል።

የፖለቲካ ጉዳዮች

የቅዱስ ጀርሜን የህይወት ታሪክ በጣም ከተወሳሰበው አንዱ ገጽታ ፖለቲካን ይመለከታል። በአንድ ወቅት በፋርስ ሻህ ፍርድ ቤት በኣንድ አነስተኛ ኣእምሮ በነበረዉና ተጠራጣሪ ገዥ ላይ ጠቃሚ ተጽዕኖ ኣሳድሮዋል፣። በሌላ ጊዜ ፈረንሳይን እንዳገለገለ ፣ ከዚያ እንግሊዝን እንደረዳ ፣ ከዚያ ለፕሩሺያ እርዳታ እንደሰጠ ፣ ከዚያ ከኦስትሪያ ፍርድ ቤት ተወካዮች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንደነበረው ፣ ከዚያ በሩሲያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት ለማደራጀት እንደረዳ ፣ ወዘተ.  . የእሱ እርምጃዎች የሚከናወኑት ከታሪካዊ ሂደቶች ግልፅ ግንዛቤ እና ጥልቅ የፖለቲካ ራዕይ እና ቅድመ እይታ ነው። እሱ ሁል ጊዜ በነገሮች ቁምነገርነት፣ በዓለም ታሪክ ትኩረት ውስጥ እና የጠፋውን ሚዛናዊነት በመመለስ ስራ ነበር የተጠመደው። ስለዚህ ፣ ንጉስ ሉዊ 15 ኛ፣ ፈረንሳይን ከጥፋት ለመታደግ በፈረንሣይ እና በእንግሊዝ መካከል ሰላምን ለማዉረድ ለቅዱስ ጀርሜን ተልዕኮ ሰጥቶታል።

እ.ኤ.አ በ 1762 በሩሲያ መፈንቅለ መንግሥት ውስጥም እንዲሁ ተሳትፎዋል፣ ምንም እንኳን በዚያ ክስተት ውስጥ ለመሳተፉ ቀጥተኛ ማስረጃዎች ባይኖሩም ፣ የመፈንቅለ መንግስቱ ሂደት በራሱ ይናገራል። ኤ. ን ባርሱኮቭ (A.N. Barsukov) በ “18ኛው ክፍለ ዘመን የሩሲያ ታሪክ ተረቶች” ውስጥ መሠረታዊው መፈንቅለ መንግሥት ያለ የእርስ በርስ ደም መፍሰስ ተከናውኗል ሲል ይገልጸዋል። በዚያን ቀን የነበሩትን የቀንና ሌሊት ክስተቶች (እ.ኤ.አ ሰኔ 28 ፣ 1762) ፣ ብናስታዉስ ውይም ብናስተነትን ፣ ድርጊቱ በፍጥነት እና በጥንቃቄ የተሰሩ የአንድ የተዋጣለት የቀዶ ጥገና ሐኪም ድርጊቶችን ይመስላሉ። ጎልተው ከሚታዩት የመፈንቅለ መንግስቱ ተሳታፊዎች መካከል ከቅዱስ ጀርሜንና ከንግስት ካትሪን 2ኛ ( Catherine II) ጋር ግንኙነት የነበራቸው የኦርሎፍ ወንድማማቾች ግሪጎር እና አሌክሲስ (Gregor and Alexis) ይገኙበታል።

ከኣድሀማ (d’Adhémar) መኳንንት ባለቤት ማስታወሻ፣ ቅዱስ ጀርሜን ፈረንሳይን ከማይቀረው ጥፋት እና የንጉሣዊውን ቤተሰብ ከሞት ለማዳን ያደረገውን ጥረት እናውቃለን። ቅዱስ ጀርሜን ፣ ሉዊ 16 ኛ እና ማሪ አንቶይኔት (Marie Antoinette) ስለ ማይቀረው አብዮት አስጠንቅቋቸው ነበር ፣ ሆኖም እነዚህ ሁሉ ጥረቶቹ ከንቱ ነበሩ።

ነቢይ ኤልዛቤት ክሌር (Prophet Elizabeth Clare) በመጽሓፉዋ ውስጥ እንዳለችው “ይህ እዉቀት ሰጪ እና ኣስቸጋሪ ትምህርት ነበር  እጅግ በጣም ጥልቅ ጥበብ ያለው ሰው ቢሆንም ፣ እጅግ የላቀ ዓላማ ያለው እና የአገሮች መነሳትና መውደቅ የሚፈጥሩ ጉዳዮችና የዓለምን ችግሮች እንዴት እንደሚፈታ ዕውቀት ያለው ቢሆንም፣ ፣ የሟቹ የሰውን ልኝ ነፃነት ማክበር ነበረበት። እሱ ምክር ሊሰጥ ይችላል  እንጂ  ትዕዛዝ  ኣይሰጥም ፣ ምክሩ ችላ ከተባለ ደግሞ ማድረግ ያለበት ትቶ መሄድ ብቻ ነው። ”

ታላቁ የመንፈሳዊ መነቃቃት

ቅዱስ ጀርሜን በመንፈሳዊ የመነቃቃት ስራ ታላቅ ተሳታፊ ነበር ፣ ስለሆነም የፍልስፍና እና የሚስጢራዊ ሕይወቱ ገጽታን ለመፈለግ፣ መርምሮ ለመረዳት እንኳን የበለጠ ምስጢራዊ እና የተወሳሰበ ነበር።

ቅዱስ ጀርሜን በጻፈው የክላሲካል መናፍስታዊ ስራው “እጅግ ቅዱስ ትሪኖሶፊያ (The Most Holy Trinosophia)”      ዘመናዊ ቋንቋና የጥንታዊ ሂሮግሊፊክስን እና ጥልቅ የፍልስፍና ይዘት ያላቸው በርካታ ግጥሞችን ተጠቅሞዋል ።

ቅዱስ ጀርሜን የምስጢር ማኅበራት መስራች ነው ፣ ሮሲክሩሲያን (Rosicrucians ) መሪ ፣ የፍሪሜሶን ፣ በወቅቱ Knights Templars የሚባሉት። በኢሳቤል ኩፐር-ኦክሌይ (Isabel Cooper-Oakley) መሠረት የፍሪሜሶን ማህደሮች ጥልቅ ጥናት በ እ.ኤ.አ 1785  በታላቁ የፓሪስ ኮንግረስ ውስጥ ከነበሩት የፈረንሣይ ሜሶኖች ተወካዮች አንዱ እንደነበረ ያሳያል።

በብዙ መንፈሳዊ ማህበረሰቦች ውስጥ ዘልቆ የገባው የማይታየው ተፅዕኖው በጣም ሰፊና ረዢም ይመስላል። እናም እነዚያን ነፃ ማህበራት በአንድላይ የሚወሃዱበትን መንገድ ይፈልግ ነበረ። በ ዘግሬት ዋይት ብራዘርሁድ  ( Great White Brotherhood)  እውነተኛ ተከታዮች ወይም መልእክተኞች እንደተከናወኑ በሚመስል፣ እነዚያ መንፈሳዊ ማህበራት የተመሰረቱት በኣንድ አይነት መሰረታዊ መርሆዎች እንደነበር መጥቀስ ተገቢ ነው። ለምሳሌ ፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮዋዊ ዘገምተኛ ለውጥ፣ ዳግም መወለድ፣ የመንስኤ እና የውጤት ግንኙነት ፣ የሕይወት ንጽህና እና በሁሉም ቦታ የሚገኘው መለኮታዊው ኃይል የሚሉት ይጠቀሳሉ።

በ “የሂማላያን ማህበረሰብ አባል”  ደብዳቤዋ ውስጥ ሄለና ሮይሪች (Helena Roerich)፣ መኳንንቱ ቅዱስ ጀርሜን ፣ የእውቀት እና የብርሃን ጠባቂ ስትል ጠቅሳዋለች። ሄ ለና ፒ ብላቫትስኪ  (Helena P. Blavatsky ) በ Theosophical Glossary ውስጥ እንደገለጸችው   “መኳንንቱ ቅዱስ ጀርሜን በእርግጠኝነት ባለፉት ምእተ ኣመታት አውሮፓ ያየችው ታላቅ ምስራዊ ፈላስፋ ነበር”

በ 18 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ቅዱስ ጀርሜን በ 100 ዓመታት ውስጥ እንደገና እንደሚመለስ ለኣደሀማዋ እመቤት (Countess d’Adhémar ) ቃል ገብቶ ነበር ። እውነትም ፣ በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ቅዱስ ጀርሜን ለቲዎሶፊካል ማህበር ምስረታ ፣ እነ ማስተር ኤል ሞሪያ፣ ፣ ማስተር ኩቱሚ ፣ እና ሄለና ፒ ብላቫትስኪን ለማገዝ መጥቶ ነበር።

እ.ኤ.አ. በ 1930 ዎቹ ፣ ወደ ሰማይ ካረገ በኃላ፣ ቅዱስ ጀርሜን ከጉይ (Guy) እና ኤድና ባላርድ (Edna Ballard) ጋር ግንኙነት ነበረው። እ.ኤ.አ. በ 1958  በተግባራዊ መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ፣ የቅዱሳን (Ascended Masters )ትምህርቶችን ለማሳተም በማሰብ “The Summit Lighthouse” በተባለው ድርጅት በኩል ከነብይ ማርክ ኤል (Mark L. Prophet) ጋር ትብብሩን ጀመረ። በማርክና በነብይ ኤሊዛቤት ክላር (Mark and Elizabeth Clare Prophet) በኩል ፣ ቅዱስ ጀርሜን የአሁኑን ጊዜ ችግሮች ለመፍታት ብዙ ጸሎቶችን እና ሜዲቴሽኖችን ኣስተምሮዋል። ከትምህርቶቹም ዉስት የቫዮሌት ነበልባልን (Violet flame | የመንፈስ ቅዱስ እሳት) ጥቅም ኣንዱ በጣም አስፈላጊ የሆነና የታወቀው ነበር።

በአሁኑ ጊዜ ፣ ቅዱስ ጀርሜን ፣ በ ዘግሬት ዋይት ብራዘርሁድ (The Great White Brotherhood) አማካኝነት ከሌሎች መምህራን ጋር በመሆን በእግዚአብሄር መልእክተኛ እመቤት Tatyana N. Mickushina በኩል መልእክት መስጠቱን ቀጥሏል።

ማስተር ቅዱስ ጀርሜን በአኳሪየስ ዘመን የበላይ ጠባቂ በመሆን ግንባር ቀደም ሆኖ መጥቶዋል።

በቀድሞው ህይወቱ ውስጥ ብዙ ሚናዎችን ተጫውቷል ። የቅዱስ ጀርሜንን ጥቂት ያለፉ የህወት ዘመኖቹን እንደሚከተሉት ተጠቅሰዋል።

የኢየሱስ እናት የማርያም ባል ዮሴፍ። ዮሴፍ ፣ በወንጌል መሠረት ፣ የንጉሥ ዳዊት ቀጥተኛ ዘር ቢሆንም ፣ ድሃ ነበር እና በናዝሬት ከተማ ውስጥ እንደ አናጢ ሆኖ ይኖርና ይሰራ ነበር። ስለ ኢየሱስ መወለድ እውነታዎች ካልሆነ በስተቀር በወንጌል ውስጥ ስለ ዮሴፍ በጣም ትንሽ መረጃ ነው የተሰጠው።

የማቴዎስ ወንጌል (ቁ 1: ም 19-24) እንደሚጠቅሰው፣ ዮሴፍ ማርያም እንደጸነሰች ኣዉቆ በስውር ሊፈታት አስቦ ነበር። ነገር ግን ዮሴፍ በሕልሙ ሊቀ መላእክት ገብርኤል ጎበኘው እና ከጋብቻቸው በፊት እንደፀነሰች ገልጾ እና ቢሆንም “ማርያምን ለማግባት አትፍራ ፣ ምክንያቱም በእርሷ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነው። ወንድ ልጅ ትወልዳለች ፤ ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ፣ ምክንያቱም እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ። ከዚያ በኋላ ፣ዮሴፍ የጌታ መልአክ ያዘዘውን አደረገ እናም ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት።

የእግዜአብሄር መልኣክ ዮሴፍን በህልሙ ሄሮድስ ኢየሱስን ለመግደል እንዳሰበ ኣስጠነቀቀው። ዮሴፍ የመልአኩን ማስጠንቀቂያ ሰምቶ ቤተሰቡን ወደ ግብፅ ወሰደ። ሄሮድስ ከሞተም በኋላ ተመለሱ።

በሕይወት ታሪኩ መሠረት ዮሴፍ ከ 12 ዓመቱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ከሄደ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በ 100 ዓመት ዕድሜው ሞተ። ስለ ዮሴፍ ከዚህ በላይ አልተጠቀሰም። ቢሆንም የአፖክሪፋ ወንጌል “የአናጢው የዮሴፍ ታሪክ” በሚል ኣርእስት የተጻፈ ታሪክ አለ።

በካቶሊክ ባህል ውስጥ ቅዱስ ዮሴፍ የአጽናፈ ዓለም ቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ሆኖ ይከበራል።

ክሪስቶፈር ኮሎምበስ (እ.ኤ.አ 1451-1506)-ክሪስቶፈር ኮሎምበስ መርከበኛ ፣ አሜሪካ የደረሰ ኤክስፕሎረር (ተጓዥ) ነበር። የተወለደው በኢጣሊያ ጄኖዋ ሲሆን በዚህ ሕይወቱ አንድ ሦስተኛውን በባህር ጉዞዎች አሳል ፎዋል።

በዘመኑ ሰዎች ገለፃ መሠረት ክሪስቶፈር ኮሎምበስ ከኣማካይ ቁመና ካላቸው ሰዎች ከፍ ያለ ፣ መልካም ቁመና ያለዉና ፈርጣማ ቅርጸ ኣካል የነበረው ሰው ነው። ቀላ ያለ ፀጉሩ በወጣትነቱ መጀመሪያ ላይ ግራጫ ሆነ ፣ ይህም ያለዕድሜው ያረጀ እንዲመስል አድርጎታል። ረዢም ፊት እና የተጋለጡ ሕያው ዓይኖች እና ቆንጆ አፍንጫ ነበረው ። ኮሎምበስ በመለኮታዊ አርቆ አሳቢነት እና የትንቢቶች ተግባራዊነት ላይ ጠንካራ እምነት አሳይቷል። እሱ ፈጣን የማስተዋል ፣ የማሳመን ጠንካራ ችሎታ እና ሁለገብ ዕውቀት ነበረው። ሁለት ጊዜ አግብቶ ነበር፣  ሁለት ወንድ ልጆችም ነበሩት። ኮሎምበስ ፣ በመጽሃፍ ቅዱስ  በዮሐንስ ራእይ ውስጥ የተጠቀሰውን እና ቀደም ሲል በኢሳይያስ አስቀድሞ የተነገረውንየአዲሷ የእግዜአብሄር መንግስት ማደሪያ (ገነት) እና የአዲሷ ምድር” ሆኖ የተሾመ  የእግዚአብሔር  መልእክተኛ እንደሆነ በትክክል ያምን ነበር።

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን በማጥናት ፣ ከተልዕኮው ጋር የተዛመዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ይጠቅሳል ፣ ይህም “የትንቢቶች መጽሓፍ” (በስፓኒሽ “ኤል ሊብሮ ዴ ላስ ፕሮፌሲያ”) በሚል የታተመው መጽሓፍ እንዲጻፍ ምክንያት ሆኗል። የእንግሊዝ ኢንሳይክሎፔዲያ እንኳን ኮሎምበስ አሜሪካን ያገኘው በከዋክብት ጥናት ላይ ተመርኩዞ ሳይሆን በትንቢቶቹ እርዳታ ምክንያት መሆኑን ይገልጻል።

ኮሎምበስ በሕይወቱ ውስጥ አራት ጉዞዎችን አድርጎዋል። የመጀመሪያው ጉዞ (እ.ኤ.አ 1492-93) ከ 90 ሰዎች ጋር በ 3  መርከቦች ስማቸው፣ “ሳንታ ማሪያ” ፣ “ፒንታ” እና “ኒና” የሚባሉ ። ከፓሎስ ፣ ስፔን ፣ እ.ኤ.አ ነሐሴ 3 ቀን 1492 ፣ የአትላንቲክ ውቅያኖስን አቋርጦ ፣ ሳርጋሶ ባህርን በማግኘት ፣ በባሃማስ ደሴት ኣከባቢ ከሚገኘው አንድ ደሴት ላይ እ.ኤ.አ በጥቅምት 12 ቀን 1492 ደርሶዋል።  ስሙንም ሳን ሳልቫዶር ብሎ ሰይሞታል ፣ በዚህ ዘመን በሳን ሳልቫዶር የክሪስቶፈር ኮሎምበስን ወደ አሜሪካ መምጣቱን ለመዘከር  ኦፊሴላዊ በዓል ሆኖዋል።

በሚቀጥሉት ጉዞዎች ወቅት ኮሎምበስ ብዙ የካሪቢያን ባህር ደሴቶችን አግኝቶዋል፣ የመካከለኛው አሜሪካን የባህር ዳርቻዎችን ዳስሶዋል። የእሱ ግኝቶች፣ የመሬቶች ቅኝ ግዛት እና የስፔን ሰፈራዎች መሠረት ሆኖዋል፣ እንዲሁም በአሸናፊዎቹ ወታደሮች ( The troops of conquistadors) “ሕንዶች” ተብለው የሚጠሩትን የአቦርጂናል ሰዎች በጭካኔ የተሞላበት ባርነት እና የጅምላ ጭፍጨፋ ሁኔታዎችን አስከትሏል።

ኮሎምበስ አሜሪካን የደረሰ የመጀመሪያው ተጉዋዥ አልነበረም። ደሴቶቹ እና የሰሜን አሜሪካ ዳርቻ ከእርሱ በፊት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በኖርስሜን (Norsemen) ተጎብኝተዋል። ሆኖም የኮሎምበስ ግኝቶች ሁለንተናዊ እና ታሪካዊ ጠቀሜታ ነበረው። አዲስ የዓለም ክፍል ስለማግኘቱ ቆይቶ በማጂላን (Magellan) ጉዞ ተረጋግጦዋል።

ፍራንሲስ ቤከን (እ.ኤ.አ 1561-1626)-ፍራንሲስ ቤከን የእንግሊዝ ፈላስፋ ፣ የሀገር መሪ ፣ ጸሃፊ ፣ እና የተሐድሶ ዘመን ድንቅ ደራሲ ነበር። በምዕራባዊው ሥልጣኔ ትልቁ ኣእምሮ ተብሎ የሚጠራው ቤከን ፣ ለሳይንሳዊ ጥያቄ እና ዘዴዎች ሰርፀታዊ ሞዴል መስራች በመባል ይታወቃል ፣ ይህም በዓለም ላይ በሳይንሳዊ ዕውቀት ሂደት ውስጥ ኣዲስ ኣቅጣጫ ያስቀመጠ ነው።

በአጠቃላይ ፣ ቤከን ሳይንስን እንደ ትልቅ ጥቅም ይቆጥረዋል ፣ ይህም “ዕውቀት ኃይል ነው”   በሚለው ዝነኛ  ጥቅስ ውስጥ እንደገለጸው በራሱ ገላጭ ነው።  በእነዚያ ጊዜያት ሳይንስ ተወዳጅ አልነበረም እናም ብዙ ተተችቷል። ቤከን ጥቃቶቹን ከመረመረ በኋላ ፣ እግዚአብሔር የተፈጥሮን ምርመራ አልከለከለም ወደሚል መደምደሚያ ደረሰ። በተቃራኒው ፣ አጽናፈ ዓለሙን (the universe) የማወቅ ፍላጎት እንዲኖረው ለሰው ልጅ ኣእምሮን ሰጥቷል። ሰዎች እውቀትን የማግኘት  መንገዶች ሁለት ብቻ እንደሁኑ መረዳት አለባቸው – የመልካም እና የክፉ እውቀትን ማግኘት፣ እና በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ነገሮችን እና ሂደቶችን ማወቅ ናቸው።

ቤከን እንደሚለው ፣ ለሰዎች መልካምን እና ክፉን ዕውቀትን ማግኘት የተከለከለ ነበር ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ አማካይነት ይህን እዉቀት ሰጦዋቸዋል። በተጨማሪም ሰው በአዕምሮው እርዳታ ፍጥረትን ማጥናትና መመርመር አለበት። ስለዚህ ሳይንስ በሰው ልጅ ግዛት ውስጥ ተገቢውን ቦታ መያዝ አለበት። የሳይንስ ሚና የሰዎችን እዉቀትና ኃይል በማብዛት ሀብታም እና ጥሩ ሕይወትን ማምጣት ነው።

ቤከን የትምህርት ዓላማው በውጫዊው ዓለም ውስጥ እራስን ለመምራት የሚያስችል እውቀት የማግኛ ትክክለኛው ዘዴ ነው ብሎ ያምናል። እሱ የሚከተሉትን ዘዴዎች እንደ ትክክለኛዎቹ ዘዴዎች ኣድርጎ ይቆጥራቸዋል – መገንዘብ (መታዘብ) ፣ ዳሰሳ ወይም ፍለጋ ፣ ሙከራ እና አጠቃላይ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ወደ ተጨባጭ ድምዳሜዎች የመድረስ ችሎታን ማዳበር። እሱም የረቀቀ እዉቀት (Mastering)፣ የመረዳት እና የልምድ ውጤት መሆኑን እርግጠኛ ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኤልዛቤት ዘመን ከሥነ ጽሑፍ ሰዎች ልሂቃን ጋር አንድ የምሁራን ቡድን በቤከን ዙሪያ ተሰበሰበ። ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ “ዘ ናይት ስ ኦፍ ዘ ሄልመት “The Knights of the Helmet”.ብለው እራሳቸዉን የሚጠሩ የምስጢር ማህበረሰብ አባላት ነበሩ። የ “ዘ ናይትስ ” ዓላማ የእንግሊዝኛ ቋንቋን በማሰራጨት እና አዲስ ጽሑፍን በላቲን ሳይሆን በእንግሊዝኛ በመፍጠር ማንኛውም እንግሊዛዊ ሊረዳው በሚችል ቋንቋ ትምህርትን የበለጠ ፍጹም ማድረግ ነበር። ቤከን መጽሃፍ ቅዱስ ለተራው ህዝብ ተደራሽ መሆን እንዳለበት ስለሚያምን፣ መጽሐፍ ቅዱስን ወደ እንግሊዝኛ (ኪንግ ጀምስ መጽሐፍ ቅዱስ) እንዲተረጎም  አነሳሽ ነበር።

እ.ኤ.አ በ 1890 ዎቹ በዊልያም ሼክስፒር ተውኔቶች የመጀመሪያ እትም እና በፍራንሲስ ቤከን ሥራዎች እንዲሁም በሌሎች የኤልዛቤት ዘመን ደራሲዎች ሥራዎች ውስጥ አንዳንድ ልዩ ሚስጥራዊ ቃላቶች (cipher texts) ተገኝተዋል። እነዚያ ጽሑፎች ቤከን ለዊልያም ሼክስፒር የተሰጡትን ተውኔቶች እንደፃፈ እና እሱ በእርግጥ የንግስት ኤልሳቤጥ( Queen Elizabeth ) እና የጌታ ሌስተር (Lord Leicester ) ልጅ መሆኑን ገልፀዋል።

ቤከን በአንድ ሳይንሳዊ ሙከራዎቹ ወቅት ጉንፋን ይዞት ነው የሞተው። ቀድሞውኑ በጠና ታምሞ ስለነበር፣ ሙከራው ስኬታማ መሆኑን ከጓደኞቹ ለአንዱ ለጌታ አሩንዴል (Lord Arundel) አሳዉቆ ነበር። ታዋቂው ምሁር፣ ሳይንስ ለሰው ልጅ በተፈጥሮ ላይ ኃይል እንደሚሰጠው እና የህይወት መሻሻልን እንደሚያመጣለት ያምን ነበር።

ኤች.ፒ. ብሌቫትስኪ (H.P. Blavatsky) “ምስጢራዊው ትምህርት ” ውስጥ እንደጻፈችው፣ በእያንዳንዱ ምዕተ ዓመት መጨረሻ መምህራን የሰውን ልጅ መንፈሳዊ እድገት ለመርዳት ሙከራ ያደርጋሉ ። እናም በማንኛውም ምዕተ-ዓመት መጨረሻ ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚሄድ የመንፈሳዊነት ኃይለኛ ማዕበል መኖሩ አይቀሬ ነው። አንድ ወይም ብዙ መምህራን በዓለም ውስጥ የዚህ መንፈሳዊነት መሪ ሆነው ይታያሉ ፣ በዚህም ለሰው ልጅ የመንፈስ ዕውቀትን ወይም ትምህርትን በከፊል ይተዋሉ። ይህ ኣባባል፣ ይህንን የላቀ ሰው እና መምህር – ቅዱስ ጀርሜንን የሚገልጽ እዉነት ነው።

ይህ ጽሁፍ በ  ሲሪየስ ኔት ድህረ ገጽ ላይ  በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈዉን  የ ቅዱስ ጀርሜን ታሪክ ጽሁፍ  ቃል በቃል ተተርጉሞ የቀረበ  የአማርኛ ትርጉም ነው። This article is a verbatim translation of the English version of a story of St. Germain from the following website  https://sirius-eng.net/liki/sen-germen.htm

ተርጓሚ መስፍን ሃጎስ ተወልደ ( ዕለት 18.10.2021)