Birhan | Spiritual Messages, Teachings & Insights.

Birhan Logo: A stylized representation of the company's name, with vibrant colors and modern design.

ስለ እኛ

ይህ ድህረ ገጽ በሰው ልጅ እና በፈጣሪ ያለዉን ዝምድና ለማሳየትና ለማቀራረብ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የዓለም ቋዋንቋዎች ከብዙ ቅዱሳን እና ኣማልእክት ሲተላለፉ የቆዩና ኣሁንም እየተላለፉ ያሉ መልዕክቶችን ለመዳሰስ እና ወደ ኣማርኛ በመተርጎም ለአማርኛ ተናጋሪዎች እንዲደርሱ ለማድረግ የተጀመረ ነው።

የምንተረጉማቸው መልክቶችም ከዚህ በፊት የኖሩ ወይም እየኖሩ ያሉ የእግዚኣብሄር መልእክተኞች ያስተላለፉትን መልእክት ወይም ትምህርቶች ምንም ሳይቀየር ወደ አማርኛ በመተርጎም ለአማርኛ ተናጋሪው ክፍል ማስነበብ ብቻ ነው። በሌሎች ዓለማት በተለያዩ ቋንቋዎች ከተሰጡት ትምህርቶች በቀጥታ ተርጉሞ ከማስተላለፍ በስተቀረ፣ በአንባቢው ላይ የአምልኮ ተጽእኖ፣ ወይም የሃይማኖት ልዩነት መፍጠር ሃሳብም ዓላማም የለንም።

በሌላው ዓለም የተላለፉ መልክቶችን ወደ አማርኛ በቀጥታ በመተርጎምና (verbatim) ወደ አማርኛ ተናጋሪው በማድረስ፣ የአማርኛ አንባቢዉን ህብረተሰብ እይታ ለማስፋት ይረዳል ብለን እናምናለን ።

በመልእክቶቹ ውስጥ የሚኖሩት ሃሳቦች ከየትኛዉም የእምነት ስርዓት ወይም መሰረታዊ የሃይማኖት ተከታዮች የተወሰደ አስተሳሰብ ኣይደለም። ከእግዜአብሄር በቀጥታ ወይም የብዙ ቅዱሳን መልእክት በቀጥታ የሚተላለፍ መልእክት ነው።

LET’S KEEP IN TOUCH!

አዳዲስ ጽሁፎቻችን እንዲደርስዎ ይመዝገቡ

የንግድ ማስታወቂያዎችን አንልክም ።